በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ክፍለ ግዛት “ሴንት ሉዊስ ፓርክ” በምትባል ከተማ የ26 ዓመት ወጣት ሶማሊያዊት የቀድሞ ስደተኛ ለከንቲባነት በመወዳደር ላይ ነች፡፡ ናዲያ መሐመድ ከተመረጠች በክፍለ ግዛቷ የመጀመሪያ ሙስሊም እና ትውልደ ሶማሊያ ከንቲባ ትሆናለች፡፡
ናዲያ በስደተኝነት ወደዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ክፍለ ግዛት መኖር የጀመረችው በአስር ዓመቷ ሲሆን ከአራት ዓመታት በፊት የመጀመሪያ ትውልደ ሶማሊያ የሴንት ሉዊስ ፓርክ ከተማ ምክር ቤት አባል በመሆን ታርክ ሰርታለች፡፡ የከንቲባ ምርጫው በመጭው ሕዳር ወር ይካሄዳል፡፡
መሐሙድ ማስካዴ ከሚኒያፖሊስ ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡