በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ መንግሥትና የዩናይትድ ስቴትስ የነዳጅ ፈላጊ ድርጅት ተወዛገቡ


የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሁሴን (ፎርማጆ)
የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሁሴን (ፎርማጆ)

የሶማልያ መንግሥት እና አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ድርጅት ባላፈው የካቲት ቱሪክ ኢስታንቡል ላይ በተደረሰበት አንድ የነዳጅ ፍለጋ ፕሮጀክት ሥምምነት ውዝግብ ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡

ሥምምንቱን የሶማልያ የነዳጅና የማዕድን ሀብት ሚኒስትር አብዲራሽድ መሀመድ አህመድ ኮስት ላይን ኤክስፕሎሬሽን ሊትድ ከተባለው ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ሪቻርድ አንደርስ ጋር የፈረሙበት ቢሆንም የሶማልያው ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሁሴን (ፎርማጆ) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሀመድ ሀስን ሮብሌ ሥምምነቱን ውድቅ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

ሁለቱ መሪዎች እንደሚሉት ውሳኔው የታገደው ሚኒስትሮችና የመንግሥት ተቋማት እየተካሄደ የሚገኘው የምክር ቤት አባላት ምርጫ ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስ ከውጭ መንግሥታትም ሆነ ድርጅቶች ጋር እንዳይፈራረሙ ከዚህ በፊት ያወጡትን ትዕዛዝ በመተላለፉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የምክር ቤቱ ምርጫ የተካሄደና ውጤቱ የተገለጸ ቢሆንም ሂደቱ የሚጠናቀቀው ምክር ቤቱ አዲስ ፕሬዚዳንት ከሚመርጥበት ከሚቀጥለው ወር በኋላ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ይህም ሆኖ ግን መንግሥት ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ሱሌማን ሞሀመድ ሥምምነቱን መርምረው ህጋዊ እምርጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸው ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የዩናይትድ ስቴትስ ነዳጅ ፈላጊው ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ አንደርሰን ለቪኦኤ ሶማልኛ ክፍል ዘጋቢ ሀሩን ማሩፍ የጣሱ መመሪያ አለመኖሩን ገልጸው ከሚኒስትሩ ጋር የተፈራረሙት ሥምምነቱ በፕሬዚዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚታወቅና የነሱ ይሁንታ መኖሩን ካረጋገጡ በኋላ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG