በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ መንግሥት በአልሻባብ ተይዘው የነበሩ ሁለት ከተሞችን አስለቀቀ


የሶማሊያ መንግሥት ኃይሎቹ በማዕከላዊ ጉሙዱግ ክፍለ ግዛት ታጣቂው ቡድን አልሻባብ ይዟቸው የነበሩ ሁለት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ተናገረ።

የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሐመድ ኑር ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል በሰጡት ቃል እንዳሉት የመንግሥቱ ኃይሎች እና የአካባቢዎቹ ተዋጊዎች ታጣቂዎቹ ያለምንም ውጊያ የለቀቋቸውን ሃራርዴሬ እና ጋልካድ ከተሞች ተቆጣጥረዋል።

ሃራርዴሬ የተባለችው ቁልፍ የባህር ጠረፍ ከተማ የባህር ላይ ዘራፊዎች ዋና መናኸሪያ ስትሆን አልሸባብ ጉልሙዱግ ውስጥ ከተቆጣጠራቸው ስፍራዎች ሁሉ በስትራተጂያዊነቷ ከፍተኛውን ቦታ የያዘች መሆኗ ተመልክቷል።

የሶማሊያ መንግሥት በተጨማሪም የታጣቂውን ቡድን የገቢ ምንጭ ለማድረቅ በሚወስደው ዕርምጃ ከቡድኑ ጋር ንክኪ ያላቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ የባንክ ሂሳቦች እና ተንቀሳቃሽ የገንዘብ ማስተላለፊያዎች መዝጋቱን አስታውቋል።

የሁለቱ ከተሞች መያዝ በማዕከላዊ ሶማሊያ በመንግሥት የጦር ሰራዊት መሪነት በታጣቂው ቡድን ላይ የተያዘው ጥቃት እየተፋፋመ መሆኑን የሚጠቁም መሆኑ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG