በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊው ፑንትላንድ ግጭት የተኩስ አቁም ሥምምነት ተደረሰ


ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች በፑንትላንድ የባህር ዳርቻ በጥበቃ ላይ
ፎቶ ፋይል፦ የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች በፑንትላንድ የባህር ዳርቻ በጥበቃ ላይ

በከፊል ራስ ገዝ በሆነቸው የሶማሊ ፑንትላንድ በሚገኙ ሁለት የጸጥታ ኃይሎች ቡድን መካከል በቦሳሶ ወደብ ለሁለት ቀና ሲካሄድ የነበረው ግጭት በተደረገው የተኩስ አቁም ሥምምነት መቆሙን የፑንትላንድ ባለሥልጣናት ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ግጭቱ የተነሳው ባለፈው ማክሰኞ በአንድ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ የጸረ ሽብር ኃይል ይደገፍ በነበረው በፑንትላንድ የደህንነት ኃይሎች ቡድን /ፒሲኤፍ/ እና በግዛቲቱ መደበኛው የደህንነት ኃይል መካከል ለሳምንታት በተፈጠረ አለመግባባት እንደነበር ተገልጿል፡፡

የሶማሊ ፑንትላንድ ፕሬዚዳንት የፒሲኤፍ ኃላፊን ኮማንደር ሞሀመድ ኡስማን ዳዮን እኤአ ህዳር 24 ለማበራረ መወሰናቸው ትልቁ የተቃውሞ መነሻ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የተኩስ አቁሙ ስምምነት የተደረሰው በአገር ሽማግሌዎች አስታራቂነት እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ከዐይን እማኞችና የህክምና ባለሙያዎች የተገኘው መረጃ በግጭቱ ቢያንስ 14 ሰዎች መሞታቸውንና ወደ 63 የሚደርሱት ደግሞ መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

ፒሲኤፍ ቀደም ሲል በዩናይትድ ስቴትስ እየተደገፈ የአልሸባብና የእስላማዊ መንግሥት ተዋጊዎችን ሲዋጋ የቆየ ልዩ የደህንነት ኃይል መሆኑን በዘገባው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG