ድሬዳዋ —
በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተከሰተውን ድርቅ ሸሽተው “ፋፋ” ን ወደ ተባለ ዞን የተሰደዱ አርብቶ አደሮች እየተደረገላቸው የሚገኘው ድጋፍ እስከቀጣይ የሚያዚያ የበልግ ዝናብ እንዲቀጥል ጠየቁ።
የሶማሌ ክልል መንግሥት እስካሁን 300 ሺ እንስሳት በድርቁ የተነሳ መሞታቸውን ገልጿል።
ከሌሎች ክልሎችና ከንግዱ ማኅበረሰብ 800 ሚሊዮን ብር የሚደርስ እርዳታ አሰባስቦ ድርቁን ለመከላከል እንዳዋለው አስታውቋል።