የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጥምረት ባለፈው ወር በተካሄደው የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ በጠባብ ልዩነት ማሸነፉን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
በአዲሱ ቅንጅታቸው ምክንያትም በፓርላማው ውስጥ ፍፁም የበላይነት ይዘው እንደሚቀጥሉ ታውቋል።
“የሪፐብሊኳ ቅንጅት” ወይም በምኅፃር ኤአርፒ የሚባለውን የራሳቸውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎችንም ያቀፈው የፕሬዚዳንቱ ጥምረት ፓርላማው ካሉት 165 መቀመጫዎች 82ቱን ማሸነፉን የሴኔጋል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሆነው የሆነው ህገመንግሥታዊ ችሎት ትናንት፤ ሃሙስ አስታውቋል።