በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴኔጋል የማኪ ሳል ቅንጅት አሸነፈ


ድምጽ ለመስጠት ከምርጫ ጣቢያቸው ውጭ ወረፋ እየተጠባበቁ
ድምጽ ለመስጠት ከምርጫ ጣቢያቸው ውጭ ወረፋ እየተጠባበቁ

ሴኔጋል ትናንት በተደረገው ምርጫ ገዥው የፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የፈጠሩት የፓርቲዎች ቅንጅት አሸንፏል፡፡ በማኪ ሳል የሚመራው ቅንጅት ከ46 የምርጫ ክልሎች ውስጥ 30ውን ማሸነፉ ተገልጿል።

ሃገሪቱን ከዚህ በፊት በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት አሚናታ ቱሬ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት የምርጫው ውጤት ለገዥው ፓርቲ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አብላጫ መቀመጫ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

የዋና ከተማዪቱ ዳካር ከንቲባና የተቃዋሚ መሪ የሆኑት ባርተለሚ ዲያስ ህዝቡ ውጤቱን እንዳይቀበልና ተቃውሞውን አደባባይ ወጥቶ እንዲያሰማ ጥሪ አድርገዋል።

የምርጫው አጠቃላይና የመጨረሻ ውጤት ምናልባት እስከ ፊታችን ዓርብ ላይታወቅ እንደሚችል ተዘግቧል። የሴኔጋል ምርጫ ተመጣጣኝ ውክልናንና ከሃገሪቱ ውጪ ከሚኖሩ ዜጎች አብዛኛውን ድምፅ ያገኙትም ይካተቱበታል።

በአፍሪካ ሴኔጋል እንደተረጋጋች ዴሞክራሲ የምትቆጠር ቢሆንም ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በሚቀጥለው ዓመት ለሦስተኛ ግዜ ለምርጫ ለመቅረብ አዝማሚያ በማሳየታቸውና ይህም ከሀገሪቱ ህገ መንግሥት ጋር የሚፃረር በመሆኑ ሥጋት ፈጥሯል።

XS
SM
MD
LG