ዋሺንግተን ዲሲ —
ልክ የዛሬ ወር ፌሊሲየን ካቡጋ ፈረንሣይ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረበ።
ይህ ከርዋንዳ ፍጅት አውራዎች አንዱ የሆን ግለሰብ ላለፉት ሃያ ዓመታት በላይ እራሱን ደብቆ ፓሪስ አቅራቢያ ይኖር ነበር።
አንዳንዶች “ዓለምአቀፍ ትሪብዩናል መቅረብ አለበት” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “የለም መረጃዎችንም፣ ማስረጃም በበቂና በቅርብ ለማግኘት እንዲቻል ወደ ኪጋሊ ይላክልን” የሚሉ ነበሩ። ሌሎች ደግሞ “ብቻ ሕግ ፊት ይቅረብ እንጂ የትም ይዳኝ” የሚሉም አሉ።
ርዋንዳ ዓለምን ባሸማቀቀ ሁኔታ ስምንት መቶ ሺህ ዜጎቿን ያጣችበትን ጅምላ የዘር ፍጅት ሃያ ስድስተኛ ዓመት እየዘከረች የምትገኝበት ጊዜ ነው።
ከጭፍጨፋው የተረፉ ዛሬ ያንን ጊዜ በሰቀቀን እና ከእንባ ጋር ያስታውሱታል።
የተያያዘው የድምፅ ፋይል የካቡጋን መያዝና ከርዋንዳም ታሪክ ቀንጨብ አድርጎ ያስታውሰናል፤ ያድምጡት።