በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩዋንዳ ሠራተኞቹን በማሰቃየት የተከሰሰው ቻይናዊ 20 ዓመት ተቀጣ


የሩዋንዳ ፍርድ ቤት ዛሬ ረቡዕ በሰጠው ውሳኔ ሠራተኞቹን በዛፍ ግንድ ላይ ጠፍሮ በማሰር ሊገርፋቸው ሞክሯል የተባለውን አንድ የቻይና ማእድን ኢንጂነር በ20 ዓመት እስራት መቅጣቱ ተነገረ፡፡

ሰዎችን በማሰቃየት የተከሰሰው ቻይናዊው ሱን ሹጂን ሁለት የሩዋንዳ ሠራተኞቹን ዛፍ ግንድ ላይ ያሰረበት የቪዲዮ ምስል ባላፈው ዓመት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ሱጂን ሁለቱ ሠራተኞ የራሱ ከሆነው ድርጅት ማዕድናትን ሰርቀዋል ሲል ተናግሯል፡፡

በሩዋንዳ የቻይና ኤምባሲ በወቅቱ የሱጂንን ድርጊት ኮንኖ መግለጫ ማውጣቱ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG