በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ባቡር ጣቢያ በሩሲያ ሮኬቶች ተመታ


በሁለት ሮኬቶች በተመታውና ክራማቶርስክ በተባለችው ከተማ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ አደጋ ደረሰ።
በሁለት ሮኬቶች በተመታውና ክራማቶርስክ በተባለችው ከተማ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ አደጋ ደረሰ።

በምስራቅ ዩክሬን በምትገኝ አንድ ከተማ ህዝብ በበዛበት የባቡር ጣቢያ ላይ በደረሱ የሩሲያ ሮኬት ጥቃቶች 30 ሰዎች ሲሞቱ 100 መቁሰላቸውን ተነገረ፡፡

በሁለት ሮኬቶች በተመታውና ክራማቶርስክ በተባለችው ከተማ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ አደጋው ሲደርስ አካባቢውን ለቀው የሚሰደዱት በሺዎቾ የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

የሩሲያ መከካለያ ሚኒስትር የባቡር ጣቢያውን ማጥቃታቸውን ቢያስተባብሉም የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከውጭ ሆነው ባብሩን ይጠበበቁ በነበሩ ሰዎች ላይ ለደረሰው ጥቃት ሩሲያን ወንጅለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን ሩሲያ በዩክሬን ሰላማዊ ሰዎች ላይ ስላደረሰቸው ግፎች በጦርነቱ እየተጎዱ ከሚገኙ አካባቢዎች የሚወጡ ዘገባዎች አንድ ቀን ተጠያቂ የሆነ ሰው ከሞስኮ እንዲወጣ ያደርጉታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG