- ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ800 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ ልትሰጥ ነው
ሩሲያ ጥቁር ባህር ላይ ያለው ትልቁ ፀረ አውሮፕላን ሚሳይል ተኳሽ መርከቧ ሞስክቫ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ከባድ ጉዳት መድረሱን እና መርከበኞቹ በሙሉ መውጣታቸውን አስታወቀች። የዩክሬን ባለሥልጣናት መርከቡ በሚሳይል ተመቷል ብለዋል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር ቃጠሎ መርከቡ በተነሳ ቃጠሎ የተከማቹ ጥይቶች ፈንድተው መሆኑን ነው ገልፆ እሳቱም ጠፍቷል። መርከቡም ባህሩ ላይ እያተንሳፈፈ ነው ብሏል። ትላልቆቹ መሳሪያዎች እንዳልተጎዱ እና መርከቡን ወደወደብ ለመውሰድ ጥረት እይተደረገ መሆኑን አክሎ ገልጿል። የኦዴሳ አስተዳዳሪ በበኩላቸው የሩሲያው የጦር መርከብ በሁለት ተውዘግዛጊ ሚሳይል ተመትቷል ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ዩክሬን ላይ የሚያደርሱት የዘር ማጥፋት ሊሆን እንደሚችል መናገራቸው አግራሞት ያጫረ ሲሆን ትናንት ዋይት ኃውስ አጠናክሮታል።
ባይደን ለዩክሬን ተጨማሪ የስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ እና ጥይት እንልካለን ብለዋል።
የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ዩክሪየን “ሁላችንም እንደምናየው በግላጭ እየተፈጸመ ስላለው ግፍ የተሰማቸውን ነው የገለጹት፥ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ህጋዊ ሂደት መታየት እንዳለበትም ተናግረዋል፥ ነገር ግን እየተፈጸመ ያለውን የጭካኔ አድራጎት ሁሉ የሚያየው ነው” ብለዋል።
አስከትለውም ድርጊቱ በምንም አይነት ስም ይጠራ የኛ አላማ ግፍ እየተሰራባቸው ያሉትን ዩክሬናውያን በዛሬው ግዙፍ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንደሚያሳየው መርዳት ነው ሲሉ አክለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ስለምትልከው አዲሱ የመሳሪያ እርዳታ ትናንት የዩክሬኑንመሪ ቮሎድሚር ዜሌንሲክን ያነጋግሯቸው ባይደን ስለተጨማሪ እርዳታው ገልጸውላቸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተመድ የሰባዊ ረድኤት ጉዳዮች ኃላፊ ማርቲን ግርፊስ የተኩስ አቁም ሥምምነት ለማሰማገል በቅርቡ ሞስኮን እና ኪቭን መጎብኘታቸው ሲታወስ የድርጅቱ ዋና ጸኃፊ ጉቲሬዝ ያ አሁን የሚሳካ አይመስልም ብለዋል።