በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በርካታ ሩሲያውያን ከሀገር ለመውጣት እየተጣደፉ ነው


ተጓዦች፤ በቤልግሬድ፣ ሰርቢያ አውሮፕላን ማረፊያ እአአ 21/2022
ተጓዦች፤ በቤልግሬድ፣ ሰርቢያ አውሮፕላን ማረፊያ እአአ 21/2022

በድጋሚ የታደሰ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቸውን ተጠባባቂ ወታደራዊ ኃይል በከፊል እንደሚያንቀሳቅሱ ትናንት ካሳወቁ በኋላ፣ በርካታ ሩሲያውያን ከሃገር ለመውጣት ትኬት ለመቁረጥ ሲጣደፉ ተስተውለዋል።

የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ 300 ሺህ የሚሆኑና የውጊያና የአገልግሎት ልምድ ያላቸውን ተጠባባቂዎች በመጀመሪያው ዙር ጦሩ እንደሚያንቀሳስ አስታውቀዋል።

የሩሲያ ድንበሮች ሊዘጉ ይችላሉ፣ ወይም ፑቲን አጠቃላይ ጥሪ ሊያደርጉ ይችላሉ በሚል ፍራቻ የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ሰማይ ነክቷል።

ፑቲን ከሰባት ወራት በፊት ጦራቸው ዩክሬንን እንዲወር ካዘዙ በኋላ፣ በርካታ ሩሲያውያን ሀገራቸውን ጥለው ወጥተዋል።

የአውሮፓ ህብረት የበረራ ማዕቀብ ከጣለ በኋላ ከቱርክ አየር መንገድ በተጨማሪ ወደ ሩሲያ አሁንም በመብረር ላይ ያለው የሰርቢያ አየር መንገድ፣ ከሞስኮ ወደ ቤልግሬድ ለሚያደርገው በረራ ለሚቀጥሉት በርካታ ቀናት ትኬት ሸጦ መጨረሱን አስታውቋል። ከሞስኮ ኢስታንቡል ወይም ዱባይ ለሚደረግ ለአንድ መንገድ የኢኮኖሚ በረራ እስከ 9,119 ዶላር እየተጠየቀ ነው።

በቤልግሬድ መሰረቱን ያደረገውና፣ ጦርነትን በመቃወም የተሰባሰቡ ሩሲያውያን፣ ቤላሩሲያን፣ ዩክሬናውያንና ሰርቦች ቡድን በትዊተር እንዳስታወቀው ከሩሲያ ወደ ቤልግራደ ያሉት በረራዎች እስከሚቀጥለው ወር አጋማሽ ድረስ ተሽጠው አልቀዋል። ወደ ቱርክ፣ ጆርጂያ እና አርሜኒያ የሚሄዱ በረራዎችም ተሽጠው አልቀዋል።

እንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፎች እንደሚያሳዩት ወደ ጆርጂያ ለማቋረጥ የሞከሩ ሰዎች ድንበር ላይ እንዲመለሱ መደርጋቸውን አስታውቀዋል። በመንግሥት የሚተዳደረው የሩሲያ ባቡር መንግድ ድርጅት ድረ ገጽ በጎብኚዎች በመጨናነቁ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።

XS
SM
MD
LG