በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን ሁለት የሩሲያ ዲፕሎማቶችን አባረረች


የቺቺንያ ተወላጅ ዘሊምካኻን ቶኒኬ ካንጎሽቪል አስከሬን
የቺቺንያ ተወላጅ ዘሊምካኻን ቶኒኬ ካንጎሽቪል አስከሬን

እኤአ 2019 በርሊን ውስጥ የተገደለው የጀርመን ዜጋ በሩሲያ ትእዛዝ የተፈጸመ ነው ብሎ የጀርመን ፍርድ ቤት ትናንት ረቡዕ በመወሰኑ፣ ጀርመን ሁለት የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከሃገሯ ማበረሯን አስታወቀች፡፡

የጀርመን ዜግነት የነበረው የቺቺንያ ተወላጅ ዘሊምካኻን ቶኒኬ ካንጎሽቪል፣ የተገደለው በጀርመን መናፈሻ ውስጥ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የጀርመን ፍርድ ቤት ሩሲያዊውን ቫዲም ክራሽኮቭን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ የእድሜ ልክ እስራት ፈርዶበታል፡፡

ቫዲም የሀሰት መታወቂያና የሚያስፈልጉት ሌሎች ነገሮች በሩሲያ ባለሥልጣናት እየተሰጠው ለሩሲያ ሲሰራ እንደነበር በፍርድ ቤት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

ሟቹ ዘሊምካንም እኤአ በ2004 ሩሲያ ውስጥ አንድ ሰላማዊ ዜጋና ፖሊስ በተገደሉበት በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በተከፈተ ጥቃት ተስታፊ መሆኑን ተነገሯል፡፡

በጀርመንት የሩሲያ አምባሳደር ጉዳዩን አስተባብለዋል፡፡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድርጊቱ “የጀርመንን ሉዐላዊነት የጣሰ ነው” ብለዋል፡፡

በጀርመን የሩሲያ አምባሳደር ስለጉዳዩ እንዲያስረዱ በጀርመን መንግሥት የተጠሩ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG