በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምዕራባውያን የሩሲያውን ዋግነር በአሸባሪነት ሊፈርጁ እየተዘጋጁ ነው


ምዕራባውያን የሩሲያውን ዋግነር በአሸባሪነት ሊፈርጁ እየተዘጋጁ ነው
ምዕራባውያን የሩሲያውን ዋግነር በአሸባሪነት ሊፈርጁ እየተዘጋጁ ነው

እንግሊዝ፣ በዩክሬኑ ወረራ፣ በከፍተኛ ደረጃ ተሳታፊ ኾኗል፣ የተባለውን የሩሲያውን የግል ቅጥር ወታደራዊ ቡድን - ዋግነርን፣ በአሸባሪነት ለመፈረጅ እየተዘጋጀች መኾኑን፣ ዘ ታይምስ ኦፍ ለንደን የተባለው የአገሪቱ ጋዜጣ፣ መንግሥታዊ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት እና ዩናይትድ ስቴትስም እንዲሁ፣ ዋግነርን ለመፈረጅ እየተነጋገሩበት እንደኾነ ተገልጿል፡፡

ይህ የሽብር ፍረጃ ርምጃ፣ ቡድኑን፣ እንደ እስላማዊ መንግሥት ወይም አልቃዒዳ፣ በተመሳሳይ ምድብ ውስጥ ይከተዋል፤ ተብሏል፡፡

የሚበዙት የዋግነር - ቅጥር ወታደራዊ ቡድን አባላት፣ ከሩሲያ እስር ቤቶች እንደተመለመሉ ሲነገር፣ ቡድኑ፥ የሩሲያን ጦርነት፣ በዩክሬኗ የባኽሙት ከተማ እያስፋፉ ስለ መኾኑ ተመልክቷል፡፡

የዩክሬንና ምዕራባውያን መንግሥታት፣ ዋግነር፥ በሩሲያ እና ዩክሬን ውጊያ፣ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎቹን አጥቷል፤ ይላሉ፡፡

የዋግነር ቅጥር ወታደሮች፥ በሶሪያ፣ በሊቢያ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ በማሊ እና ሱዳንን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች መሠማራቱ ተገልጿል፡፡

ዋግነር፣ የመንግሥታትን ደኅንነት ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ሲገልጽ፣ በአጸፋው ደግሞ የማዕድን ሀብቶችን እንደሚጠይቅና የሩሲያን ቀጣናዊ የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት እንደሚንቀሳቀስ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG