በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማነው ነዳጅ ከሩሲያ ላይ እየገዛ ያለው?


ማነው ነዳጅ ከሩሲያ ላይ እየገዛ ያለው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00

ማነው ነዳጅ ከሩሲያ ላይ እየገዛ ያለው?

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት እያካሄደች እና ዓለም አቀፋዊ ማዕቀብ እያለባትም ወደ ውጪ የምትልከው የነዳጅ ምርት ምንም አልቀነሰም። በተቃራኒው ሀገሪቱ በሚያዚያ ወር ወደ ውጪ የላከችው የነዳጅ ምርት ከጦርነቱ በፊት ከላከችው ይበልጣል።

የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ ማለት ደግሞ ሞስኮ ገንዘብ እያጋበሰች ነው ማለት ነው።

ይህ ደግሞ አውሮፓ አዲስ የነዳጅ ማዕቀብ በሩሲያ ላይ መጣልን እንድታስብበት ምክንያት ሆኗል። እስከ አሁን ተጥለው ያሉ ማዕቀቦች ሞስኮን እየጎዳት አይደለም።

አውሮፓ አብዛኛውን ነዳጅ ከሩሲያ የምታገኝ በመሆኑ አሁን ያንን ለማካካስ ሌሎች አካባቢዎችን ማማተር አለባት። ይህ ደግሞ ቀላል አይሆንም። በሁሉም አካባቢ ያለውን የነዳጅ ዋጋም የበለጠ እንዲያሻቅብ ያደርጋል።

በአሜሪካ ድምፅ በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።

XS
SM
MD
LG