በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካን ፓርቲ ብሄራዊ ጉባዔ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካን ፓርቲ ብሄራዊ ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል። ጉባዔው በከፊል በአካል በከፊል ደግሞ በርቀት ሊከናወን ዝግጅት ተደርጓል።

ሰሜን ካሮላይናዋ ሻርለት ከተማ በሚከፈተው የፓርቲው ጉባዔ ላይ ተወካዮቹ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በመጭው ምርጫ ፓርቲያቸውን ወክለው እንዲወዳደሩ በይፋ ይመርጧቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ለአራት ቀናት በሚዘልቀው ጉባዔ ላይ በየዕለቱ ንግግር እንደሚያደርጉና የፓርቲያቸውን ዕጩነት ከዋሽንግተን እንደሚቀበሉ ተገልጿል።

የሪፐብሊካን ፓርቲው ተወካዮች ትናንት በቴሌቪዥን ቀርበው ያደረጓቸውን ገለፃዎች ተመርኩዞ አራሽ አራብሳዲ ያጠናቀረውን ዘገባ ይዘናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካን ፓርቲ ብሄራዊ ጉባዔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:41 0:00


XS
SM
MD
LG