በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓኪስታን የቀድሞ ጠ/ሚ/ር የፀረ መንግሥት ተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ አቀረቡ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካኻን
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካኻን

የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካኻን ትናንት ዕሁድ በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ለመጠየቅ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ በአገሪቱ መዲና ኢስላማባድ መጠነ ሰፊ የሆነውን የፀረ መንግሥት ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚመሩ አስታወቁ፡፡

ካኻን ትሪክ ኢኢንሳፍ ወይም ፒት የተሰኘው ፓርቲያቸው ደጋፊዎችና ፓኪስታናውያን በሙሉ ከረቡዕ ጀምሮ በሚደረገው ተቃውሞ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ ወደ መቀመጥ አድማ እያደገ በመሄድ ጥያቄያቸው ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከክሬኬት ተጫዋችነት ወደ ፖለቲካሰው የተቀየሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ካኻን አራት ዓመት ከቆዩበት ሥልጣናቸው የተወገዱት ባለፈው ወር ተቃዋሚዎቻቸው የምክር ቤት አባላት በነፈጓቸው የመተማመኛ ድምጽ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የእርሳቸው ዋነኛ ተቃናቃኝ የነበሩት ሸኽባዝ ሸሪፊ የተቃዋሚዎቹ ጥምረት መሪ ሆነው የተኳቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

የ69 ዓመቱ ኢምራን ካኻን ዩናይትድ ስቴትስ ከተቃዋሚዎች ጋር በመመሳጠር ከሥልጣን እንዲወገዱ ያደረጓቸው መሆኑን ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ ከሰዋል፡፡

የዩናይትድስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኔድ ፕራይስ በዚህ ወር መግቢያ ላይ በሰጡት መግለጫ “ፕሮፖጋንዳና የተዛቡ የሀሰት መረጃዎች ከፍተኛ ዋጋ በምንሰጠው ከፓኪስታን ጋር ያለንን ግንኙነት ጨምሮ በመካከላችን ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ እንቅፋት እንዲሆንብን አንፈልግም” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG