በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እየተደበደቡ የታሰሩት የቀድሞው የፓኪስታን ጠ/ሚኒስትር ልዩ ፍ/ቤት ቀረቡ


እየተደበደቡ የታሰሩት የቀድሞው የፓኪስታን ጠ/ሚኒስትር ልዩ ፍ/ቤት ቀረቡ
እየተደበደቡ የታሰሩት የቀድሞው የፓኪስታን ጠ/ሚኒስትር ልዩ ፍ/ቤት ቀረቡ

ትላንት በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ኻን፣ በሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ክሥ ዛሬ ልዩ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

የ70 ዓመቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የተያዙት፥ ሽብርን፣ የአገር ክሕደትንና ሙስናን ጨምሮ የተመሠረቱባቸውን ክሦች በሚመለከተው ችሎት ላይ ለመገኘት እየተዘጋጁ ሳሉ ነበር፡፡

በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው ኢወጋዊ ኀይሎች፣ እየደበደቡ በሥፍራው ሲጠባበቁ ለነበሩት የፀረ ሙስና ባለሥልጣናት ያስረከቧቸው መኾኑን ጠበቃቸው ተናግረዋል፡፡

የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ክሦች የተመለከተው ልዩ ፍርድ ቤት፣ በታሰሩበት የመዲናዋ የፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃ ጋራ የተሠየመ መኾኑ ተመልክቷል፡፡

እስሩን ተከትሎ፣ በዋና ከተማዋ እና በሌሎችም ከተሞች፣ በኻን የፖለቲካ ፓርቲ ታሪክ - ኢ - ኢንሳፍ (Tehreek-e-Insaf) ደጋፊዎች፣ ወዲያውኑ ተቃውሞ እና ሁከት ተቀስቅሷል፡፡

ተቃዋሚዎች እና የዐይን እማኞች እንደተናገሩት፣ የጸጥታ ኃይሎች በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ጥይት ተኩሰው፣ ቢያንስ አንድ ሰው ሲገድሉ ብዙዎችን አቁስለዋል፡፡

በመዲናዋ ኢስላማባድ እና በአካባቢዋ ያሉ በርካታ የዜና ማሠራጫዎች፣ የተቃውሞ ሰልፎቹን አልዘገቡም፡፡ ተቃዋሚዎች፣ በመንግሥት ተከልክለው ነው፤ ሲሉ አለመዘገቡን ኮንነዋል፡፡ ለተቃዋሚዎቹ ውንጅላ ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት ባለሥልጣን አልተገኘም፡፡

የተቃውሞ ሰልፎቹን ተከትሎ፣ የፓኪስታን መንግሥት፣ በዋና ዋና ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ሙሉ በሙሉ ከልክሏል፡፡

የመንግሥቱ የቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣናት፣ በኢስላማባድ እና በሌሎችም በርካታ ከተሞች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን አቋርጧል፡፡ ትዊትር፣ ፌስቡክ የመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ተዘግተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG