በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ የፀጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል


አቶ ኃይሉ አዱኛ
አቶ ኃይሉ አዱኛ

የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ ዐዋጅ ከታወጀ ወዲህ ከሁለት ሺህ በላይ በሚሆኑ በክልሉ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

የኦሮምያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ እንደገለፁት በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡድኑ ታጣቂዎች ሲማረኩ፤ ለአባገዳዎችም እጃቸውን የሰጡ አሉ።

በዚህ ዙርያ ራሳቸውን "የኦሮሞ ነጻነት ጦር" መንግሥት ደግሞ "ሸኔ" ከሚላቸው ታጣቂዎች አመራሮች የተሰማ ነገር የለም።

በሌላ በኩል በተፈጥሮ አደጋ እና በሰው ሰራሽ አደጋ ለተፈናቀሉ የተለያዩ የክልሉ ዞኖች ነዋሪዎች እርዳታ እየደረሰላቸው መሆኑን አቶ ኃይሉ አዱኛ ገልጸዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ የፀጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00


XS
SM
MD
LG