በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህገወጥ የሰዎች አስተላላፊው ትውልደ ኤርትራዊ ጆን ሀብቱ ተያዘ


የስደተኞች መብት ተሟጋችና የራድዮ አዘጋጅ ትውልደ ኤርትራ ስዊድናዊት ሜሮን እስጢፋኖስ
የስደተኞች መብት ተሟጋችና የራድዮ አዘጋጅ ትውልደ ኤርትራ ስዊድናዊት ሜሮን እስጢፋኖስ

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክሶች በኔዘርላንድ ፖሊሶች ሲታደን የነበረው ጆን ሀብታ፣ አካ ጆን ወይም ኦባማ እየተባለ በተለያየ ስም ይጠራ የነበረው ጆን ሀብቱ ከኢንተርፖል ጋር በተደረገ ክትትል ባለፈው ሳምንት ኬንያው ውስጥ መያዙ ተሰማ፡፡

የደች ዜግነት ያለው ጆን መሰረቱ ከኤርትራ ሲሆን እንግሊዝ አገር ውስጥ ንብረት ያፈረ፣ በኔዘርላንድ ተወንጅሎ በሌለበት በፍርድ ቤት የጥፋተኝነ ውሳኔ የተላለፈበት ሰው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የስደተኞች መብት ተሟጋችና የራድዮ አዘጋጅ የሆነች ትውልደ ኤርትራ ስዊድናዊት ሜሮን እስጢፋኖስ ለቪኦኤ እንደተናገረችው፣ የጆን መታሰር ለብዙዎቹ ህግ ወጥ የሰዎች አስተላላፊዎች መልዕክት፣ ሰዎችን እያሰቃዩ በአየገሩ በነጻነት ለሚዘዋወሩትም ትምህርት ነው ብላለች፡፡

እንደ ሜሮን ገለጻ ጆን በዋነኝነት ኤርትራውያን ስደተኞችን እየተከታተለ ወደ አውሮፓና አሜሪካ አሻግራችኋለሁ በሚል በነፍስ ወክፍ ወደ 20ሺ ዶላር እየተቀበለ በፊሊፒንስ፣ ማሌዥያ ሲንጋፑር እና ሌሎች የእስያ አገሮች ውስጥ ይጥላቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG