በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማፍያ አለቃ ነች የተባለች ናይጂሪያዊ ለጣሊያን ተላልፋ ተሰጠች


ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ፤ ናይጀሪያ
ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ፤ ናይጀሪያ

ሴቶችን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወርና በሴትኛ አዳሪነት በማሠማራት በጣሊያን ፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለች ናይጄሪያዊ ለጣሊያን ተላልፋ መሠጠቷን የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ከአቡጃ፣ ናይጄሪያ ወደ ሮም የተወሰደችውና በሌለችበት በፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለችው ጆይ ጄፍ የ13 ዓመታት እስር የጠብቃታል፡፡

የ48 ዓመቷ ጆይ በጣሊያን በጥብቅ ከሚፈለጉ ጥቂት ሴቶች አንዷ የነበረች ሲሆን፣ በናይጄሪያ ከማፍያ ዋና ሰዎች አንዷ ነች ተብሏል፡፡ ላለፉት 13 ዓመታት በጣሊያን ፖሊስ ስትፈለግ ነበር፡፡

ሴቶችን ወደ ጣሊያን፣ ስፔንና ኔዘርላንድ በማዘዋወርና በግዳጅ በሴትኛ አዳሪነት በማሠማራት ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ሲሉ መርማሪዎች ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG