ዋሺንግተን ዲሲ —
የናይጄሪያ ጦር አዛዥ በናይጄሪያ ከእስላማዊ መንግሥት አራማጆች ጋር ግንኙነት ያለውና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረው የቡድኑ መሪ አቡሙሳብ አልባርናዊ መገደሉን ተናገሩ፡፡
አቡ ሙሳብ በትክክል ስለመገደሉ ከገለልተኛ ወገን የተሰጠ ማረጋጋጫ የሌለ ሲሆን፣ የናይጄሪያው የጦር አዛዥ ጀኔራል ለኪ ኢራቦርም ምንም ዓይነት ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡
መግለጫው የተሰጠው የቦኮሃርም መሪ የነበረው አቡባከር ሼካኡ መገደሉ በተነገረ ከአምስት ወራት በኋላ ነው፡፡