በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ አየር መንገዶች በነዳጅ ዋጋ ምክንያት በረራ እያቆሙ ናቸው


ፎቶ ፋይል፦ ሌጎስ አውሮፕላን ማረፊታ
ፎቶ ፋይል፦ ሌጎስ አውሮፕላን ማረፊታ

ብዛት ያላቸው የናይጄሪያ አየር መንገዶች በነዳጅ ዋጋ መወደድ ምክንያት ከዛሬ ጀምረው ላልተወሰነ ጊዜ በረራ በማቆም ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ አንዳንዶቹ የአየር መንገዶች የነዳጅ እጥረትን ምክንያት በማድረግ በረራዎች መሰረዝ ወይም ማዘግየት በመጀመራቸው የሃገር ውስጥ በረራዎች ሲስተጓጎሉ ቆይተዋል።

ዘጠኝ አየር መንገዶችን የሚወክለው የናይጄሪያ አየር መንገዶች ማኅበር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሊትር ከአንድ መቶ ዘጠና ናያራ ወደሰባት መቶ ናያራ ማለትም አንድ ዶላር ከስድሳ ዘጠኝ ሳንቲም ማሻቀቡን ገልጿል።

አያይዞም ለስላሳ ደቂቃ በረራ ወጪው በእጥፍ ጨመሮ 120, 000 ናያራ በመግባቱ ከአየር መንገዶቹ አቅም በላይ እንደሆነ አመልክቷል።

ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ ጨምሮ አየር መንገዶች እና ተጓዦች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አስከትሏል።

XS
SM
MD
LG