በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ዋና ጸሃፊ ናይጄሪያ ገቡ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በአፍሪካ የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል በዛሬው ዕለት ለሁለት ቀናት ጉብኝት ናይጄሪያ ገብተዋል፣ በቆይታቸው ከናይጄሪያ መሪዎች የሚነጋገሩ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ጉተሬዥ በናይጄሪያ ቆይታቸው እኤአ በ2011 አቡጃ ውስጥ በእስላማዊ አማጽያን የቦምብ ጥቃት በደረሰበት የተባበሩት መንግሥታት ህንጻ ውስጥ የተሰው ሰዎችን በስፍራው ተገኝተው ያስባሉ ተብሎ ተነገሯል፡፡

ዋና ጸሃፊ በትናንትናው እለት በኒጀር ከፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙም ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ሽብርተኝነት ለመዋጋት ተጨማሪ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

ባላፈው እሁድ ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋርም፣ በዳካር ተገናኝተው ተነጋግረዋል፡፡

በወቅቱም ባደረጉት ጥሪ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደባቸው፣ በቡርኪናፋሶ፣ ጊኒና ማሊ የሚገኙ አምባገነን መሪዎች ሥልጣንን ለሲቪሎች በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ማሳሳባቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG