በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያው የባቡር ጥቃት 168 ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም


ፎቶ ፋይል - አዲስ የተጠናቀቀው የአቡጃ-ካዱና የባቡር መስመር ሐምሌ 21/2016
ፎቶ ፋይል - አዲስ የተጠናቀቀው የአቡጃ-ካዱና የባቡር መስመር ሐምሌ 21/2016

የናይጄሪያ ምድር ባቡር ጣቢያ ኃላፊዎች ባላፈው ሳምንት 8 ሰዎች በተገደሉበት የታጣቂዎች ጥቃት 168 ሰዎች እስካሁን ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ አስታወቁ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ታጣቂዎች ከአቡጃ ወደ ካዱና ይጓዝ በነበረው የመንገደኞች ባብሩ ላይ የተኩስ ጥቃት በማድረስ ያልታወቁ ሰዎችን አግተው ሲወስዱ ባብሩን ማፈንዳታቸው ተነገሯል፡፡

የናይጄሪያ ምድር ባቡር ሥራ አመራር ድሬክተር ፌደት ኦኪሂራ ባላፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ በቤተሰቦቻቸው የሰሙት 22 ሰዎችና ሌሎች 146 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ለኮሚሽኑ መረጃ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ሰዎቹ የተጠለፉ መሆናቸውን ባይረጋግጡም ባላፈው ዓርብ ተጠርጣሪዎቹ አሸባሪዎች ያነጋገሯቸው መሆኑን አንዳንዶቹ ቤተሰቦች ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

አብዛኛ ጥፋት በታጣቂ ወረበሎች ላይ ያረፈ ሲሆን እኤአ መጋቢት 28 ባደረሱት ጥቃትም የአቡጃን ካዱናን የባብሩ መስመር በቦምብ በማጋየት ባቡሩ ዝግ እንዲል ካደረጉ በኋላ መንገደኞቹ ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተነገሯል፡፡

በናይጄሪያ የደህንነት ጉዳዮ ተንታኝ አቤነዘር ኦዬታኪን እንዲህ ብለዋል

"በየቀኑ አሸባሪዎች የሚደቅኑብንን እንዲህ ያሉ ፈተናዎችን መቋቋም አለመቻላችን በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡"

ናይጄሪያ ታጣቂ ወረበሎችን ለዓመታት ስታዋጋ የኖረች ሲሆን በተለይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካዱና የተባለው ክፍለ ግዛቱ የበለጠ ተጎጂ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ሰላማዊ ዜጎችን የሚያግቱ ሰዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ባልታወቁ ቁጥሮች የሚደውሉ ሲሆን የናይጄሪያ መንግሥትን ይህን ለመከላከል የቴሌኮም ኩባን ያዎች አድራሻቸው ያልታወቁ ጥሪያዎች እንዳያስተላልፉ ማዘዛቸው ታውቋል፡፡

ባለሙያዎች ግን ይህ እምርጃ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የራሱ ተጽእኖ እንድሚኖረው ይናገራሉ፡፡

XS
SM
MD
LG