በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ቅዳሜ ትመርጣለች


ናይጄሪያውያን አገሪቱን ለ8 ዓመታት የመሩትን ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪን ለመተካት በመጪው ቅዳሜ ምርጫ ያደርጋሉ፡፡
ናይጄሪያውያን አገሪቱን ለ8 ዓመታት የመሩትን ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪን ለመተካት በመጪው ቅዳሜ ምርጫ ያደርጋሉ፡፡

ናይጄሪያውያን አገሪቱን ለ8 ዓመታት የመሩትን ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪን ለመተካት በመጪው ቅዳሜ ምርጫ ያደርጋሉ፡፡

የቡሃሪን ወንበር ለመውሰድ 18 ዕጩዎች የቀረቡ ቢሆንም፣ ተንታኞች ግን ሦስት ከፍተኛ ተፎካካሪዎች እንዳሉ በመናገር ላይ ናቸው፡፡

ባለጸጋውና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የ76 ዓመቱ አቲኩ አቡባካር ቀዳሚ ተፎካካሪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ የተቃዋሚው ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲው አቲኩ አቡባካር ከዚህ በፊት አምስት ግዜ ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ አሶ ሮክ የተሰኘውን የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ለመቆጣጠር ለ6ኛ ግዜ እየሞከሩ ነው፡፡

የ70 ዓመቱ ቦላ ቲንቡ ‘ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረስ’ የተሰኘውን ፓርቲን በመወከል ቀርበዋል። ቲንቡ የሌጎስ የቀድሞ አገረ ገዢ ሲሆኑ፣ “የከተማ ልጅ” አንዳንዴም “የሌጎስ የነፍስ አባት” ሲሉ ይጠሯቸዋል።

የሠራተኛ ፓርቲውና የ60 ዓመቱ ፒተር ኦቢ በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡ ደጋፊዎቻቸው ማኅበራዊ ሚዲያውን በሚገባ የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ኢኮኖሚውን ሊያሻሽሉ የሚችሉት እርሳቸው ብቻ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡

ናይጄሪያውያን በተጨማሪም በቅዳሜው ምርጫ የተወካዮች ም/ቤትንና የህግ መወሰኛ ም/ቤት አባላትን ይመርጣሉ።

ናይጄሪያውያን የሚመርጡት አገሪቱ በአክራሪዎችና ተገንጣዮች ጥቃት እየደረሰባት፣ የተዳከመ ኢኮኖሚ ባለበትና ድህነት በተንሰራፋበት ወቅት በመሆኑ ለለውጥ ያለው ጉጉት ከፍተኛ ነው።

XS
SM
MD
LG