በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ዛምፋራ ክፍለ ግዛት ነዋሪዎች እንዲታጠቁ ፈቃድ ሊሰጥ ነው


ናይጄሪያ ዛምፋራ ክፍለ ግዛት
ናይጄሪያ ዛምፋራ ክፍለ ግዛት

የናይጄሪያ ዛምፋራ ክፍለ ሀገር ነዋሪዎች ታጥቀው ራሳቸውን እንዲጠብቁ ፈቃድ እንደሚሰጥ ባለሥልጣናቱ ገለጹ።

ለዚህ አዲስ እርምጃ ምክንያት የሆነው በታጣቂዎች እና በአማጺ ቡድኖች በሚታመሰው በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ነዋሪው ራሱን መጠበቅ እንዲችል መሆኑን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል። በተጠቀሰው የናይጄሪያ አካባቢ የታጠቁ ወንጀለኛ ቡድኖች አዘውትረው ዘረፋ እንደሚፈጽሙ እና ማስለቀቂያ ለማስከፈል ሰዎችን እንደሚጠልፉ ዘገባው አመልክቷል።

በቅርቡም ካዱና ውስጥ ታጣቂዎች በሁለት አብያተ ክርስቲያን ባደረሱት ጥቃት ስምንት ሰዎችን መግደላቸው እና አርባ የሚሆኑ ሰዎችን መጥለፋቸው ይታወሳል። በተደጋጋሚ የሚደርሰው ጥቃት እና መንግሥቱ ለአስር ዓመታት ከአክራሪ እስላማዊ ቡድኖች ጋር ሲካሄድ የቆየው ውጊያ የሀገሪቱን የጸጥታ ኃይሎች አቅም እየሸረሸረ መሆኑ ተገልጿል።

የዛምፋራ ክፍለ ግዛት የህዝብ ግንኙነት ኮምሽነር በሰጡት ቃል መሳሪያ ታጥቀው ራሳቸውን ለመጠበቅ ለሚፈልጉ እና አስፈላጊውን ሁኔታ ለሚያሟሉ አምስት መቶ ሰዎች ፈቃድ በመስጠት እንጀምራለን ብለዋል።

XS
SM
MD
LG