በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ጊዜያቸው ሊያልፍ የተቃረበ 1 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን አስወገደች


ናይጄሪያ የአገልግሎታቸው ጊዜ ሊያልፍ የተቀራበ 1 ሚሊዮን የአስትራዚንካ የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒቶችን አስወገደ፣ አቡጃ፤ ናይጀሪያ
ናይጄሪያ የአገልግሎታቸው ጊዜ ሊያልፍ የተቀራበ 1 ሚሊዮን የአስትራዚንካ የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒቶችን አስወገደ፣ አቡጃ፤ ናይጀሪያ

ናይጄሪያ የአገልግሎታቸው ጊዜ ሊያልፍ የተቀራበ 1 ሚሊዮን የአስትራዚንካ የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒቶችን ማስወገዷን ትናንት ረቡዕ በተሰጠ መግለጫ አስታወቀች፡፡

የናይጄሪያ መሠረታዊ የጤና አጠባበቅ ልማት ተቋም ኃላፊ ፌይዘል ሸሄቢ የጤና ባለሥልጣናት ያን ከማድረግ ውጭ ምንም አማራጭ አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ኃላፊው በመግለጫቸው የበለጸጉ አገሮች ለናይጄሪያ መድሃኒቱን የሰጡት ብዙ ጊዜ አከማችተው ካቆዩ በኋላ የመጠቀሚያቸው ጊዜ ሊያበቃ ሲቃረብ ነው ብለዋል፡፡

206 ከሚጠጋው የናይጄሪያ ህዝብ የተከተበው 2 ከመቶ ብቻ መሆኑን ሲገለጽ የጤና ባለሥልጣናቱ እስከ ሩብ የሚደርሰውን ህዝብ እስከመጭው የካቲት ለማስተክብ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳ ክትባት መድሃኒቶችን ለመውሰድ ማንገራገር ቢኖርም የተከተቡ ሰዎች ብዛት ባላፈው ሳምንት ውስጥ በእጥፍ እየጨመረ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

ፈጣን ተስፋፊነቱ የተነገረለት አዲሱ የኦሚክሮን ቫይረስ ዝርያ፣ ባለፈው ህዳር ከታየ ወዲህ፣ ለኮቪድ-19 የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በ500 ፐርሰንት መጨመሩ ተነግሯል፡፡

በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ብቻ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ውስጥ 2ሺ123 ተጋላጮች መመዝገባቸውም ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG