በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ የትዊተር እገዳዋን አነሳች


የናይጄሪያ መንግሥት የትዊተር እገዳ ማንሳቱን ካወጀ በኋላ ጋዜጦች የመወያያ ርዕስ አድርገውታል፤ አቡጃ፣ ናይጄሪያ፣ እአአ ጥር 13/2022
የናይጄሪያ መንግሥት የትዊተር እገዳ ማንሳቱን ካወጀ በኋላ ጋዜጦች የመወያያ ርዕስ አድርገውታል፤ አቡጃ፣ ናይጄሪያ፣ እአአ ጥር 13/2022

የናይጄሪያ መንግሥት ለሰባት ወራት በትዊተር ላይ ጥሎ የነበረውን የእግዳ ማዕቀብ ያነሳ መሆኑን አስታወቀ፡፡

እገዳው የተጣለው አንድ የብሎግ ዌብሳይት የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ቡሃሪ ያስተላለፉት የትዊት መልዕክት ከሰረዘ በኋላ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ከተቋቋመው ኮሚቴ በቀረበ ሀሳብ መሰረት እገዳው የተነሳው በፕሬዚዳንቱ ፈቃድ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

አፍሪካው ውስጥ ትልቁን የህዝብ ብዛት ባለው አገር ገበያውን እንዳያጣ የሰጋው ትዊተር በናይጄሪያው ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቶ ታክስ እየከፈለ ለአገሪቱ ባለሥልጣናት የሚያደርጉት ቅርብ ክትትል ባልተለየበት ሁኔታ ሥራውን እንዲሰራ የተፈቀደለት መሆኑን የናይጄሪያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አመልከቷል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትዊተር ላይ በተጣሉ ቅድመ ሁኔታዎች ያለውን ስጋትና ተቃውሞ የገለጸ ሲሆን ትዊተር ምን ያህል የተሰጠውን ቅድመ ሁኔታ ተቀብሎ እንደሚስራ ግልጽ አይደለም ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG