በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ የአየር መንገድ ሠራተኞች አድማ መቱ


በናይጄሪያ የአውሮፕላን ጣቢያ ሠራተኞች የሁለት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ተሳፋሪዎች እየተጉላሉ ነው፡፡
በናይጄሪያ የአውሮፕላን ጣቢያ ሠራተኞች የሁለት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ተሳፋሪዎች እየተጉላሉ ነው፡፡

በናይጄሪያ የአውሮፕላን ጣቢያ ሠራተኞች የሁለት ቀናት የሥራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው፣ አየር መንገዶች በረራቸውን ሲሰርዙ፣ በሺሕ የሚቆተሩ መንገደኞች መጉላላት ደርሶባቸዋል፡፡

ሰባት የሚሆኑ የአውሮላን ጣቢያ ሠራተኞች ማኅበራት አድማውን የጠሩት መንግሥት ስምምነት ላይ በተደረሰው መሠረት የአውሮፕላን ጣቢያ የሥራ ሁኔታን የሚያሳየውና በቅርቡ የተጠናቀረው ሪፖትርት ይፋ ባለመሆኑ እና በናይጄሪያ ዝቅተኛ የክፍያ መጠን የሆነውን በወር 65 ዶላር መንግሥት ሊከፍል ባለመቻሉ ነው ተብሏል፡፡

መንግስት ጥያቄያቸውን የማይመልስ ከሆነ ላልተወሰነ ግዜ አድማቸውን እንደሚቀጥሉ ማኅበራቱ አስታውቀዋል፡፡

በናይጄሪያ የአውሮፕላን ጣቢያ የሠራተኞች አድማ የተለመደ ነው፡፡

የሥራ ሁኔታው አመቺ አለመሆኑንና አየር ምንገዶችም እየጨመረ በመጣው የነዳጅ ዋጋ ምክንያት ፈተና ውስጥ ገብተዋል ሲሉ ሠራተኞቹ ይናገራሉ፡፡

አድማው በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ለሁለተኛ ግዜ መደረጉን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG