በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት "12 ሚሊዮን ህጻናት ት/ቤት መሄድ ፈርተዋል" አሉ


የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡኻሪ፣ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ልጆች፣ ጂሃዲስቶቹና ታጣቂዎቹ ወንጀለኞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆች ወደሚታገቱባቸው ትምህር ቤቶች ለመሄድ ፈርተዋል ሲሉ ተናግሩ፡፡

በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ህጻናትን ከትምህር ቤት ማገት የተጀመረው እኤአ በ2014 በሰሜን ናይጄሪያ በበኮሃራም ታጣቂዎች የተፈጸመው የ276 ልጃገረዶች ጠለፋ ነው፡፡

ቡኻሪ አቡጃ ውስጥ በትምህርት መስክ ስላለው ደህነነት በተዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ባሰሙት ንግግር “ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ትምህር ቤቶችን በማጥቃት የሚደረገው ጠለፋ ተስፋፍቶ ቀጥሏል” ብለዋል፡፡

በሰሜን ምዕራብና መከካለኛው ናይጄሪያ ትምህርት ቤቶችን ኢላማ የሚያደርጉ ታጣቂዎች እየበዙ ሲሆን ካለፈው ታህሳስ ወዲህ ከ1ሺ በላይ ተማሪዎችን መጥለፍና ማገታቸው ተነግሯል፡፡

"በዚህ የተነሳ" ይላሉ ፕሬዚዳንቱ "ባሁኑ ወቅት ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት እጅግ ስለተሸበሩ፣ ወደ ትምህር ቤት መሄድ ፈርተዋል፡፡"

ባለሙያዎች ደግሞ “ትምህርታቸውን ያለጊዜው የሚያቁርጡህጻናት ለሚጠብቃቸው ያለ እድሜ ጋብቻ ይጋለጣሉ፡፡ በማለት ያስጠነቅቃሉ፡፡ በርካቶቹ ህጻናት ከጠለፊዎቻቸው ጋር በሚደረግ ድርድር ይለቀቃሉ፡፡

ቡኻሪ“ይሁን እንጂ የታገቱ ልጆች የሚለቀቁ ቢሆንም፣ በጠለፋው ወቅት የተፈጸመባቸው ነገር በጭንቅላታቸው ውስጥ ተቀርጾ ለረጅም ጊዜ ይቆያል፡” ብለዋል፡፡

የጸጥታው ኃይሎች በየጊዜው ትልቅ አሰሳ የሚያደርጉ ቢሆንም፣ ከቦታው ስፋት የተነሳ ኃይል ስለሚበታትን፣ ሁኔታውን መቆጣጠርና በፍጥነት ጨርሶ ለማስቆም አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG