በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞዛምቢኩ ግጭት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተፈናቀሉ ነው


በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ግዛት በነዳጅ በበለጸገችው ካቦ ደልጋዶ ክፍለ ግዛት በተነሳው ግጭት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለስደት መዳረጒ ተነገረ፡፡ ግጭቱ የተነሳው ከአንድ ዓመት በፊት በአካባቢ መንቀሳቀ የጀመሩት ጅሃዲስቶች በሚያደርሷቸው ጥቃቶች መሆኑ ተነገሯል፡፡

የተባበሩ መንግሥታት ድርጅት ትናንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግሥታዊ ያልሆኑ ታጣቂዎች በሚያደርሷቸው ተመሳሳይ ጥቃቶች ካለፈው ጥር አንስቶ እስከ መጋቢት አጋማሽ ወር ድረስ ወደ 30 ሺ የሚጠጉ ሰላማዊ ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

የአመጽ ጥቃቱ ከተጀመረ እኤአ ከ2017 ጀምሮ ወደ 735 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውንና አብዛኞቹ አስቸኳይ እርዳታ የሚሹ መሆኑን ያመለከተው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመንከባከብ ትልቅ የገንዘብ እጥረት መኖሩን አመልክቷል፡፡

የተባባሩት መንግሥታ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን እንደገለጸው ከሚያስፈልገው 36ሚሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተገኘው 11 ከመቶ ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG