በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞስኮ በድሮን ተመታች


የድሮን ጥቃት ተከትሎ ጉዳት የደረሰብትን አፓርታማ ሲመረምር
የድሮን ጥቃት ተከትሎ ጉዳት የደረሰብትን አፓርታማ ሲመረምር

ዩክሬን ሞስኮ ላይ በርካታ የድሮን ጥቃቶች አድርሳብኛለች፤ ስትል ሩሲያ ክስ አሰማች። ይኹን እንጂ፣ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፥ ወደ ከተማው የተቃረቡት ሁሉም ድርኖች መደምሰሳቸውን ገልጿል፡፡

የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌይ ሶብያኒን፣ ዛሬ ማለዳ በደረሰው የድሮን ጥቃት፣ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውንና አንደኛው ሆስፒታል መግባቱን ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ሁለት የመኖሪያ ቤት አፓርትመንቶች ላይ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች፣ ሕንጻዎቹን ለቀው ቢወጡም፣ ከቆይታ በኋላ መመለሳቸውን ተገልጿል፡፡በጥቃቱ የሞተ ሰው አለመኖሩ ተመልክቷል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ፣ በሩሲያ ላይ የሚካሔዱ የድሮን ጥቃቶች እየጠነከሩ መጥተዋል፡፡

ኒዮርክ ታይስም ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት፣ ዩክሬን፥ በዚኽ ወር መጀመሪያ ላይ በክሬምሊን አቅራቢያ ከደረሰው የድሮን ጥቃት ጀርባ አለችበት፤ ብሎ ያምናል፡፡

ዩክሬን፣ በሩሲያ ውስጥ ባሉ ዒላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸም መጀመሯን በይፋ አምና አልተቀበለችም፡፡

ጥቃቱን የመረመረው የሩሲያ አጣሪ ኮሚቴ፣ በርካታ ድሮኖች ተመትተው መውደቃቸውንና ስብርባሪዎቻቸው መጠነኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ጠቅሷል፡፡

“ተመትተው ወድቀዋል፤” ስለተባሉት ድሮኖች ብዛት ግን፣ ኮሚቴው አልገጸለም፡፡

የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩን የጠቀሱ በስም ያልተገለጹ ምንጮች፣ በሩሲያ ተመትተው የወደቁ ድሮኖች፣ ዐሥር እንደኾኑ ተናግረዋል፡፡

ከሩሲያ የደኅንነት ምንጮች፣ “ጥሩ መረጃዎችን ያገኛል፤” የተባለው ቤዛ የተባለው የቴሌግራም ቻናል፣ ሞስኮን ያጠቁት ድርኖች 25 እንደኾኑ ጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG