በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞሮኮ የፍልሰተኞችን እስራት አስረዘመች


ፎቶ ፋይል፦ የስፔን ግዛት የሆነችውን መሊላን ከሞሮኮ የሚለየው አጥር እአአ 2/3/2005
ፎቶ ፋይል፦ የስፔን ግዛት የሆነችውን መሊላን ከሞሮኮ የሚለየው አጥር እአአ 2/3/2005

በሞሮኮ የሚገኝ ይግባኝ ፍ/ቤት ባለፈው ሰኔ ወደ ስፔን በኃይል ለማቋረጥ ሞክረዋል ያላችው ፍልሰተኞች ላይ የተሰጠውን ቅጣት ወደ ሦስት ዓመት ከፍ አደረገ።

በአብዛኛው ሱዳናውያን የሆኑ 2 ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ባለፈው ሰኔ ሞሮኮን ከስፔን ጋር በሚያገናኘውና ወደ አውሮፓ በመሬት ለመሻገር ካሉት ሁለት ብቸኛ አማራጮች መካከል አንዱ የሆነውን ኬላ በኃይል ወረው መሊላ ወደተባለችው የስፔን ግዛት ለማቋረጥ ሲሞክሩ ከጠባቂዎች ጋር በተፈጠረ ግብግብ 23 ፍልሰተኞች ሞተዋል። የሰብዓዊ መብት ቡድኖች የሟቾቹን ቁጥር 37 ያደርሱታል።

በሃይል ለመሻገር በተደረገው ሙከራ ተሳትፈዋል የተባሉ 13 ፍልሰተኞች ባላፈው ነሓሴ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ቢቀጡም፣ የይግባኝ ፍ/ቤቱ ስድስት ወር ተጨማሪ ቅጣት ጥሎባቸዋል ሲሉ የፍለሰተኞቹ ጠበቃ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የሞሮኮ ባለሥልጣናት እንደሚሉት በግብግቡ 140 ፖሊሶች ተጎድተዋል።

ከዛ ክስተት ወዲህ በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጥተዋል።

XS
SM
MD
LG