በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌዴራል ሰራተኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ግዴታ ነቀፌታ አስነሳ


የዩናይትድ ስቴትስ ሚሲሲፒ ክፍለ ሀገር አገረ ገዢ ቴት ሪቭስ
የዩናይትድ ስቴትስ ሚሲሲፒ ክፍለ ሀገር አገረ ገዢ ቴት ሪቭስ

የዩናይትድ ስቴትስ ሚሲሲፒ ክፍለ ሀገር አገረ ገዢ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለፌዴራሉ መንግሥት ሰራተኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም ግዴታ ማድረጋቸው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የታለመ ሳይሆን በሰራተኞቹ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው ሲሉ ነቀፌታ አሰሙ።

ከነዋሪዎች ቁጥር አኳያ ከዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ሀገሮች ከፍተኛው በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ያላት ሚሲሲፒ መሆኗ ተጠቁሟል።

ሃገረ ገዢው ቴት ሪቭስ ነቀፌታውን ያሰሙት ትናንት ለሲኤንኤን ቴሌቭዢን በሰጡት ቃል ነው።

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ግዴታው ፕሬዚዳንቱ የሚሲሲፒን ነዋሪዎች ጨምሮ ታታሪ ሰራተኞች አሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ከመከተብ እና የቤተሰባቸውን የሚመግቡበትን ስራቸውን ከማጣት አንዱን እንዲመርጡ ስለሚፈልጉ ለዚያ ብለው የሰነዘሩት ጥቃት ነው ብለዋል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ባጠናቀረው መረጃ መሰረት ሚሲሲፒ ውስጥ ከመቶ ሽህ ሰው ውስጥ ሦስት መቶ ስድስት ሰው በኮቪድ ምክንያት ለህልፈት ተዳርጓል።

በሌላ ዜና የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ ባወጣው አዲስ ጥናት በጥናቱ ከተካተቱ ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ከሚያውቁ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የህመሙ ስሜት እስከ ሁለት ወር ድረስ እንደቆየባቸው መናገራቸውን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG