በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ፤ ወታደሮች በጂሃዲስቶች ተገደሉ


ማሊ ውስጥ ተሲት በምትባል ከተማ ባለፈው ዕሁድ ድሮንና መድፎችን ሳይጠቀሙ አልቀሩም በተባሉ እስላማዊ ቡድኖች የተወሳሰበ ጥቃት 42 ወታደሮች መገደላቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

በወታደሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት ለአሥር ዓመታት ከሰሜን እስከ ደቡብ ከዚያም አልፎ እስከ ቡርኪና ፋሶና ኒዠር የተስፋፉትን አማፅያን ስትታገል በቆየችው ማሊ የበዛው ደም የፈሰሰበት መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በዕሁዱ ግጭት 17 ወታደሮችና አራት ሲቪሎች መገደላቸውን፣ 22 ወታደሮች መቁሰላቸውንና “አሸባሪዎች” ያሏቸውን 37 ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን የጦር አዛዦቹ ተናግረዋል።

የማሊ መንግሥት በድሮን፣ በከባድ ጦር መሣሪያዎች፣ በፈንጂዎችና በተሽከርካሪዎች በመደገፍ ጥቃቱን አድርሰዋል ያላቸውን “በታላቁ ሰሃራ የእስላማዊ መንግሥት” ተዋጊዎችን ወንጅሏል።

XS
SM
MD
LG