ዋሽንግተን ዲሲ —
ወታደሮቹ በያዝነው ሳምንት የሀገሪቱ ፕረዚዳንት ቡባካር ከይታ ከስልጣን እንዲወርዱና መንግስታቸውን እንዲበትኑ ማስገደዳቸው ያሚታወቅ ነው።
አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የዜና አገልግሎት በዘገበው መሰረት ቃለ-መጠይቁ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ሲሉ ጆናታን ትላንት ማታ ተናግረዋል።
የምዕራብ አፍሪቃ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ECOWAS መልእክተኞች ከስልጣን ከተወገዱት ፕረዚዳንትና በወታደሮቹ ከተያዙት ሌሎች የመንግስትና ወታደራዊ ባለስልጣኖች ጋርም እንደተነጋገሩ ታውቋል።
“ፕረዚዳንት ከይታን አይተናቸዋል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት” ሲሉ ጆናታን መናገራቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
የወታደሮቹ ቃል አቀባይ ኢስማየል ዋጉም ንግግሮቹ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄዱ ነው ከሚለው ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።
መልእክተኞቹ ማሊ የሄዱት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ተወላጆች መፈንቅለ መንግስት ያካሄዱትን ወታደሮች ለመደገፍ ሰልፍ ባደረጉበት ማግስት ነው።