በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ ወታደራዊ መንግሥት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አከሸፍኩ አለ


ፎቶ ፋይል፦ የማሊ ዋና ከተማ ባማኮ
ፎቶ ፋይል፦ የማሊ ዋና ከተማ ባማኮ

የማሊ ወታደራዊ በስም ባልጠራው የምዕራብ ሀገር የሚደገፉ የጦር ሰራዊት መኮንኖች ባለፈው ሳምንት ያደረጉትን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አከሽፈናል አለ።

በመንግሥቱ ቴሌቭዥን የተነበበው መግለጫ ለውጥ ጠል የሆኑ ጥቂት የማሊ መኮንኖች እና ባለሌላ ማዕረግ ወታደሮች ያሉበት ቡድን ባለፈው እአአ ግንቦት 11 መንግሥት ሊገለብጡ ሞክረው ነበር ብሏል።

ሙከራውን ያደረጉት በአንድ ምዕራብ ሀገር ድጋፍ ነው ያለው መግለጫው በዝርዝር አላብራራም። የታሰሩ ሰዎች እንዳሉም ገልጿል። በዋና ከተማዋ ባማኮ እና በሀገሪቱ ድንበሮች ላይ የፀጥታ ጥበቃ አጠናክረናል ሲልም አክሎ አስታውቋል።

ማሊ ውስጥ እአአ ከ2020 ነሃሴ ወር ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደ ሲሆን የጦር ሰራዊቱ በህዝብ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታን መንግሥት ገልብጧል።

በጦር ኃይሉ የሚመራው የማሊ መንግሥት ከአክራሪ እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በሚያካሂደው ውጊያ አጋሩ የነበረችውን ፈረንሳይን ትቶ ከሩሲያ ጋር የቅርብ ትስስር ፈጥሯል።

XS
SM
MD
LG