በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ ሦስት የተመድ የሠላም አስከባሪ ጓዶች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል - ማሊ ውስጥ የተመድ የሠላም አስከባሪ ተልእኮ ወታደሮች በጋኦ፣ ማሊ ጎዳናዎች ላይ።
ፎቶ ፋይል - ማሊ ውስጥ የተመድ የሠላም አስከባሪ ተልእኮ ወታደሮች በጋኦ፣ ማሊ ጎዳናዎች ላይ።

ትናንት ማሊ ውስጥ መሬት ውስጥ የተቀበረ ፈንጂ ከተሳፈሩበት ተሽከርካሪ ላይ ባደረሰው አደጋ ሦስት የሠላም አስከባሪ ጓዶቹ ሲገደሉ ሌሎች ሦስት ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ከአል-ቃይዳና ከአይሲስ ጋር ግኑኝነት ያላቸው የእስልምና አክራሪዎች ላለፉት አስርት ዓመታት ማሊ ውስጥ ጥቃት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

የተመድ ቃል-አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለዜና ሰዎች እንደነገሩት፣ ሠላም አስከባሪዎቹ አደጋው በደረሰባቸው ወቅት በሰሜን ማሊ የተቀበሩ ፈንጂዎችን በመፈለግና በመለየት ሥራ ላይ ነበሩ።

ሦስቱ የተጎዱት ሰዎች በተመድ የህክምና ሆስፒታል እየታከሙ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ለተመድ የሠላም አስከባሪ ጓዶች በማሊ አስቸጋሪ ሁኔታ ነው ያለው ያሉት ቃል አቀባዩ፣ በዚህ ዓመት ብቻ 12 የሠላም አስከባሪ ጓዶች በተነጣጠረባቸው ጥቃት ተገድለዋል ብለዋል።

በማሊ የተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል ከተመደበበት እአአ ከ2013 አንስቶ 174 የሠላም አስከባሪ ጓዶች በተቃጣባቸው ጥቃት ተገድለዋል። በዚህም የተነሳ ማሊ ለተመድ የሠላም ጥበቃ ጓዶች በዓለም አደገኛዋ ቦታ ሆናለች።

XS
SM
MD
LG