ዋሽንግተን ዲሲ —
በቅርቡ መንፈንቅለ መንግሥት በተካሄዳበት ማሊ፣ የሽግግር መንግሥቱ፣ የ15ቱ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ህብረት መልዕከተኛ ፣ በ72 ሰዓት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ፡፡
የማሊ መንግሥት ለትእዛዙ የሰጠው ምክንያት መልዕክተኛው “ኃላፊነታቸውን የማይመጥን ሥራ ይሠራሉ” የሚል ነው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ ሁለት ጊዜ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደባት ማሊ፣ ሥልጣን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንዲተላለፍ፣ ጫና በማሳደር ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡