በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማላዊ 225 ሰዎችን ከገደለው ፍሬዲ በኋላ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠየቀች


ማላዊ 225 ሰዎችን ከገደለው ፍሬዲ በኋላ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠየቀች፡፡
ማላዊ 225 ሰዎችን ከገደለው ፍሬዲ በኋላ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ጠየቀች፡፡

የማላዊ ፕሬዚዳንት "ፍሬዲ" በሚል ስያሜ የተጠራውና በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ከፍተኛ አውሎ ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ ላደረሰው “የተፈጥሮ ጉዳት” ዓለም አቀፉ እርዳታ እንዲደረግ ተማጸኑ፡፡

የሁለት ሳምንት የሀዘን ጊዜ ያወጁት ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቸክዌራ ትናንት ረቡዕ ባሰሙት ተማጽኗቸው “ እዚህ እያስተናገድን የምንገኘው ውድመት በእጃችን ካለው ጥሪትና አቅም የበለጠ” ነው ብለዋል፡፡

መንግሥት በአደጋው ለተጎዱ በ10ሺዎች ለሚቆጠሩ የማላዊ ዜጎች የሚውል የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ቃል ገብቷል፡፡

በአደጋው በትንሹ 225 ሰዎች መሞታቸውና በብዙ መቶዎች መቁሰላቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ ደቡባዊ ምዕራብ አፍሪካ የባህር ዳርቻን፣ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የመታው ፍሬዲ፤ በሞዛምቢክና ማላዊ ውስጥ 290 ሰዎች ሲገድል ከፍተኛ ሞትና ውድመት ማድረሱ ተመልክቷል፡፡

በሰዓት 8ሺ ኬሜትር የተጓዘው አደገኛው ነፋስ ትናንት ረቡዕ የህንድ ውቅያኖስን ካቋረጠ በኋላ ውሃ ላይ በማረፍ፣ እንደገና ወደ ጎዳቸው የአፍሪካ አገሮች ለሁለተኛ ጊዜ በመመለስ ጉዳት ማድረሱ ተመልክቷል፡፡

በይፋ ባይመዘገብም በዓለም ረጅም ጊዜ የቆየው ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ መሆኑ የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG