በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማላዊ በኮሌራ ወረርሽን ተመታለች


የማላዊ ካርታ
የማላዊ ካርታ

የክትባት እጥረት ባለበትና የዝናቡ ወቅትም በተቃረበበት በዚህ ወቅት፣ ማላዊ ለረጅም ግዜ አይታ በማታውቀው አስከፊ የወባ ወረርሽኝ ተመታለች።

የኮሌራ ታማሚዎችን ለመንከባከብ የተወሰኑ የጤና ጣቢያዎች ተለይተው ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

ታማሚዎች በየቀኑ እንደሚጎርፉና፣ የጤና ረዳቶችም ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ እንደሆነ ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

ችግሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደረገው ደግሞ በዓለም ደረጃ የኮሌራ ክትባት እጥረት መከሰቱ ነው ተብሏል።

ባለፈው ወር የዓለም ጤና ድርጅት ለኮሌራ አንድ ክትባት ብቻ እንዲሰጥ ወስኗል። የኮሌራ ክትባት ውጤታማ ለመሆን ሁለት ክትባት ያስፈልገዋል ሲሉ ባለሙያዎች ይሟገታሉ።

አገሪቱ ከዓለም አቀፉ የክትባት ኅብረት የተረከበችውን 2.9 ሚሊዮን ክትባት ገና አላሰራጨችም።

በአገሪቱ እየመጣ ያለው ክረምት ችግሩን እንዳያባብሰው ተሰግቷል።

XS
SM
MD
LG