በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመንግሥት የሚደገፈው የሊቢያ ሚሊሻ የቀረበበትን የግድያና ማሰቃየት ውንጀላ አስተባበለ


የሊቢያ ካርታ
የሊቢያ ካርታ

ሊቢያ ውስጥ በመንግሥት የሚደገፈውና ከፍተኛ ሥልጣን አለው የሚባለው የሚሊሻ ቡድን በግድያ፣ በማሰቃየት፣ አስገዳጅ የጉልበት ሥራ የቀረረበትን ውንጀላ ያስተባበለ ሲሆን፣ ህጉን እንደሚያከብር አስታውቆ፣ ሪፖርቱን ባቀረበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላይ ክስ እንደሚመስረት አስታወቀ፡፡

አምነስቲ ባለፈው ረቡዕ (SSA) ወይም የመረጋጋት ድጋፍ ሰጭ ባለሥልጣን የተባለውን አካል፣ ህገወጥ ግድያዎች፣ የዘፈቀደ እስራት፣ ስደተኞችን በዘፈቀደ እያፈነ ማሰር፣ በአስገዳጅ ሥራ እና ዘግናኝ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ጨምሮ፣ በበርካታ ጥሰቶች ወንጅሎታል፡፡ ባለሥልጣኑ ግን የተባለውን የሊቢያን ህግ የሚያከብር መሆኑን አስታውቆ አባላቱ ለሚፈጽሟቸው የትኛውም ህገ ወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው አስታውቋል፡፡

ቡድኑ አምነስቲ በሊቢያ መንግሥትና ኦፊሴላዊ ተቋማቱ ላይ የሚያካሂደውን የስም ማጥፋት የመከላከል ህጋዊ መብቱን በመጠቀም ክስ የሚመሰርት መሆኑንም ገልጿል፡፡ ሊቢያ በአሁኑ ወቀት እንደገና በሁለት መንግሥታት የተከፈለች አገር መሆኗን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG