ዋሽንግተን ዲሲ —
ሊብያ ውስጥ በተለይም ታርሁና ከተማ ላይ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የጂምላ መቃብሮች መገኘታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተረሽን ክፉኛ ማስደንገጡን ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።
ከሊብያ መዲና ትሪፖሊ 65 ኪሎሜትር ርቃ የምትገኘው ታርሁና የጀነራል ኻሊፋ ሐፍታርና የወታደራዊ ሃይላቸው ፅኑ መሰረት እንደነበረች በቅርቡ ግን በሀገሪቱ መንግስት እጅ መግባትዋ ታውቋል።
በጉዳዩ ግልጽና ሰፊ ምርመር ተድርጎ ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የተባበሩት መንግስታ ድርጂቱ መሪ ጥሪ ማድረጋቸውን ቃል አቀባያቸው Stephane Dujarric ተናግረዋል።
የጂምላ መቃብሮቹ ጥበቃ ተደርጎላቸው የአስከሬኖቹ ማንነት ተለይቶ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሰጥና ለህልፈታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ እንዲጣራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚረዳ መናገራቸውን ቃል አቀባያቸው Dujarric ገልጸዋል።