በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባለሙያዎች የሰሜን ኮሪያ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬሎች አስጊ ናቸው ይላሉ


ፎቶ ፋይል፦ የሚሳየል ሙከራውን ሰዎች በቲቪ ሲመለከቱ።
ፎቶ ፋይል፦ የሚሳየል ሙከራውን ሰዎች በቲቪ ሲመለከቱ።

ባለሙያዎች የሰሜን ኮሪያ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬሎች በቀላሉ ሊከታተሏቸውና ሊቀለብሷቸው የማይችሉ በመሆናቸው ደቡብ ኮሪያን ለሰሜን ኮሪያ ሚሳዬል ጥቃት የተጋለጠች አድርጓታል ሲሉ ተናገሩ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ካነጋገራቸው ባለሞያዎች መካከል በሚድልበሪ ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም በሞንቴሪ የሚሳዬል ባለሙያ የሆኑት ጀፍሪ ለዊስ ይህ እንዳይሆን ደቡብ ኮሪያ፣ ሰሜን ኮሪያ ገና ጥቃቱ ለመሰዘንር እንዳሰበች አስቀድማ ከማምከን የተሻለ ሌላ አማራጭ የላትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባለሙያው ለዊስ ትኩረት ከተደረገበት የሚሳዬሉ ፍጥነት ይልቅ ትልቁ አደጋው ሚሳዬሉን በአየር ላይ እንደተፈለገው መዘወር የሚቻል በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ገና ሳይነሳ አስቀድሞ የሚመታ እንኳ እንዳይሆን በተንቀሳቃሽ ቦታዎች የሚነሳና አድራሻውን በቀላሉ መሰወር የሚችል፣ በዚያ ላይ ጸረ ሚሳዬል መሳሪያ የተገጠመለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንኪት ፓንዳ የተባሉ ሌላው የኒዩክለየር ፕሮግራም ተመራማሪም ደቡብ ኮሪያ አስቀድሞ የማመከኛውን ሚሳዬል መጠቀሟ የስሌት ስህተት ቢያመጣ ትልቅ አደጋ ሊያስከትል መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱም ኮሪያዮች በሚያደርጓቸው የሚሳዬል እሽቅድምድም አንዳቸው ቀድመው ሊሰሩት በሚችሉት ስህተት ከትልቅ አደጋ ውስጥ ሊያስገባቸው እንደሚችል ፓንዳ ተናግረዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ ጸረ ሚሳዬሎችን በመትከል ብቻ ስንት ቦታ ልትከላከል ትችላለች በማለት የጠየቁት ብሩስ ቤነት የተባሉት በራንድ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የመከላከያ ተመራማሪ ደግሞ ደቡብ ኮሪያ ሚሳዬሎቹን ከመነሻው ሳይነሱ ማምከን የሚያስችላትን ቴክኖሎጂ ላይ ማተኮር አለባት ብለዋል፡፡

ብሩስ ይሁን እንጂ ሰሜን ኮሪያ ያሏት ሚሳዬሎች እነ ዩናይትድ ስቴትስ እነሩሲያና ቻይና ሀይፐር ሶኒክ (ከድምጽ አስምት ጊዜ በላይ የሚፈጥኑ) ብለው እንኳ የማይጠሯቸው በጣም የተጋነኑ ናቸው ብለዋል፡፡

ይህም ሆኖ በዚህ ወር ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ ከጣለችባት ወዲህ እንኳ ሰሜን ኮሪያ ሁለት ጊዜ የሚሳዬል ሙከራዎች ማድረጓ ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG