በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ድንበር አካባቢ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 13 ሰዎች ሞቱ


ኬንያ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል፣ ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ ይጓዝ በነበረ የህዝብ አውቶብስ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ 13 ሰዎች ሞቱ።
ኬንያ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል፣ ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ ይጓዝ በነበረ የህዝብ አውቶብስ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ 13 ሰዎች ሞቱ።

ኬንያ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል፣ ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ ይጓዝ በነበረ የህዝብ አውቶብስ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ 13 ሰዎች መገደላቸውና ፖሊስም አንደኛውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

ፍንዳታውን ተከትሎ የተኩስ ድምጽ መሰማቱን የዓይን እማኞች ለኬንያ መገናኛ ብዙሃን ተናገረዋል፡፡

ለጥቃቱ ወደያውኑ ኃላፊነቱም የወሰደ አካል አለመኖሩ ተነግሯል፡፡

ይሁን እንጂ አደጋውን ያደረሰው የሶማልያው አልሸባብ ሊሆን እንደሚችል መገመቱን ሪፖርተራችን ሞሀመድ የሱፍ ከናይሮቢ በላከው ዘገባ አመልክቷል፡፡

እኤአ በ2015 አልሸባብ በተመሳሳይ መንገድ ላይ ይጓዙ በነበሩ ተሸክርካሪዎች ላይ አደጋ በመጣል አንድ የፖሊስ ባልደረባን ጨምሮ ሁለት ሰዎችን መግደሉ ተጠቅሷል፡፡

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እዚያው ላሙ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ፣ የፍርድ ቤት ዳኞች በሚጓጓዙበት ተሽከርካሪ ላይ፣ የአልሸባብ አባላት የጥይት ምስል ቀብተው መሄዳቸውን ፖሊስ አስታውቆ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG