በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ የተቃዋሚ መሪ የተቃውሞ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ


በኬንያ የተቃውሞ ሰልፎች
በኬንያ የተቃውሞ ሰልፎች

በኬንያ፣ በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስተዳደር ሥር፣ የኑሮ ውድነት ማሻቀቡን በመቃወም የተጀመረው ፀረ መንግሥት ሰልፍ እንዲቀጥል፣ የተቃዋሚው መሪ በአስተላለፉት ጥሪ መሠረት፣ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እና በሌሎችም ከተሞች ሰልፉ ዛሬም ሊቀጥል ይችላል፤ በሚል የጸጥታ ኃይሎች ዝግጅት ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

በትናንትው ዕለት ፖሊሶች፣ የተቃውሞ ሰልፎችን የከለከሉ ቢኾንም፣ የተቃዋሚ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ተቃውሞው እንዲቀጥል አበረታተዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ፣ በሰልፈኞች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ፣ አንድ ሰው ሲገደል ብዙዎች መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡

የኬንያ የባቡር አገልግሎት፣ ትናንት በአወጣው መግለጫ፣ “ከዐቅም በላይ በኾነ ምክንያት፣ የነገ ሰኞ መደበኛ የባቡር አገልግሎት ተሰርዟል፤” ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ ራይላ ኦዲንጋ፣ ኬንያውያን፣ ሰኞ እና ኀሙስ ጎዳና ላይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

XS
SM
MD
LG