በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ያልተለመደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ


በኪቤራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ ሲሰጥ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ፣ እአአ 8/9/2022
በኪቤራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ ሲሰጥ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ፣ እአአ 8/9/2022

ያልተለመደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ ኬንያውያን በጠዋት የምርጫ ጣቢያዎች ከመከፈታቸው በፊት ሰልፍ ይዘው ታይተዋል።

ያልተለመደ የሚያደርገው የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የረጅም ጊዜ ተቃዋሚያቸውንና አሁን ለፕሬዝደንትነት የሚወዳደሩትን ራይላ ኦዲንጋን መደገፋቸው ሲሆን ሌላው ተወዳዳሪ ተቀማጩ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ደግሞ ልክ ለቤተ መንግሥቱ አዲስ የሆኑ ወይም ራሳቸውን “ባይተዋር” አድርገው ማቅረባቸው ነው።

ራይላ ኦዲንጋ በግንባር ካሉ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዱ ሲሆኑ ለሩብ ምዕት ዓመት ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደሩ ቆይተዋል።

“አሸነፍኩም ተሸነፍኩም የተፎካካሪዎቼን እጅ እጨብጣለሁ” ብለዋል ኦዲንጋ። ምክንያቱም አሉ “ራሴን ራይላ ኦዲንጋን ከምወደው በላይ ኬንያን እወዳለሁ።”

ተፎካካሪያቸው ዊሊያም ሩቶ ደግሞ ከልጅነት ጀምሮ የመጡበትን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ከከባድ ኑሮ ጋር ለሚታገለው አብዛኛው ኬንያዊ አስታውስው የፖለቲካ ሥልጣንን ጠቅልሎ ከያዘው ንዑስ ክፍል መላቀቅ እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት ተናግረዋል።

“ሲበቃ በቃ ነው። ነፃነት እየመጣች ነው። ህዝብ ከ“ስውር መንግሥት” ነፃ ይወጣል። የኬንያ ህዝብ ከሥርዓቱ ነፃ ይወጣል፤ ማንም ኬንያዊ ወደ ኋላ የማይተውበት ሃገር ይኖረናል” ብለዋል ዊሊያም ሩቶ።

[የዛሬውን የኬንያ ምርጫ እየተከታተልን ማቅረብ እንቀጥላለን]

XS
SM
MD
LG