በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ በመንግሥት ላይ የሚደረገው ተቃውሞ ቀጥሏል


በኬንያ፣ የታክስ ጭማሪን በመቃወም ሰልፍ በወጡ የናይሮቢ ነዋሪዎች ላይ፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ
በኬንያ፣ የታክስ ጭማሪን በመቃወም ሰልፍ በወጡ የናይሮቢ ነዋሪዎች ላይ፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ

በኬንያ፣ የታክስ ጭማሪን በመቃወም ሰልፍ በወጡ የናይሮቢ ነዋሪዎች ላይ፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል።

በተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ በተጠራው ሰልፍ ላይ፣ ነዋሪዎች እንዳይገኙ ፖሊስ አግዶ የነበረ ሲኾን፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች በብዛት በሚገኙባት ማታሬ በምትባል የመዲናዪቱ ክፍል፣ ተቃዋሚዎች ድንጋይ ሲወረውሩ፣ ፖሊስ በአጸፋው አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል። በወደብ ከተማዋ ሞምባሳም፣ ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ ተቃዋሚዎችን በትኗል፤ ተብሏል።

ባለፈው ሳምንት በነበረ ተቃውሞ፣ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዛሬ ጠዋት ከተካሔደው የተቃውሞ ሰልፍ ቀደም ብሎ፣ ለሰልፉ ጥሪ ያደረጉት ወገኖች፣ “ባለሥልጣናትን አላሳወቁም፤ ሰልፉ ሕገ ወጥ ነው፤” በሚል፣ የፖሊስ አዛዡ፣ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በሰልፉ እንዳይሳተፉ አስጠንቅቀው ነበር።

ባለፈው ዓርብ፣ ፖሊስ፣ በኦዲንጋ የመኪና አጀብ ላይ ያነጣጠረ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፤ ሲል፣ የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል። ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ፣ ፖሊስ በሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፤ ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ተናግረዋል።

የአገሪቱ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ፖሊስ ፈጽሞታል ስለተባለው የጭካኔ ተግባር፣ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የ‘አዚሚዮ ትብብር’ የተሰኘው የራይላ ኦዲንጋ ፓርቲ፣ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶን ፖሊሲዎች በመቃወም በየሳምንቱ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG