በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ መንግሥት የኬንያ አየር መንገድን እዳ ሊከፍል ነው


ፎቶ ፋይል፦የኬንያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ናይሮቢ፤ ኬንያ
ፎቶ ፋይል፦የኬንያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ናይሮቢ፤ ኬንያ

የኬንያ መንግሥት ከ800ሚሊዮን ዶላር በላይ እዳ ያለበትን የኬንያን አየር መንገድ እዳ እንደሚሸፍንና በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ወደ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የበጀት ድጋፍ በማድረግ እንደሚታደገው አስታወቀ፡፡

መንግሥት ለአየር መንገዱ የሚሰጠውን 800 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ያሰበው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ በመበደር እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

የኬንያ መንግሥት በቅርቡ በሰጠው መግለጫ እንደተመለከተው መንግሥት ከአየር መንገዱ የ49 ከመቶ የባለቤትነት ይዞታ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የበጀት ድጎማ በማድረግ አየርመንገዱ ከእዳ ለመታደግ መሞከሩ ትክክለኛ እርምጃ ስለመሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ጥያቄ ማንሳታቸው ተዘግቧል፡፡

የኬንያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከፉኛ የተጎዳ መሆኑን ገልጸው ካለፈው ጥር እስከ ሰኔ ወር ብቻ 100 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ የደረሰበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እኤአ በ2020ም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ አየር መንገዱ 130 ሚሊዮን ዶላር መክሰሩን ሥራ አስፈጻሚው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በናይሮቢ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ጄምሲ ሺክዋቲ የኬን ያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚፎካከር መሆኑን ገልጸው እኤአ በ1980ዎቹ ይበልጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ በከፊል ወደ ግል ይዞታ እንዲዛወር መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ በመንግሥት ይዞታ ጸንቶ ከቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለየ እጣ የገጠመው መሆኑን ገልጸው አሁን ተወዳዳሪ የሚሆንበት እድል ያልተዘጋ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አንዳንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አየር መንገዱ ራሱን መልሶ እንዲያዋቅር ሠራተኞችን እንዲቀንስ አዳዲስ ኮንትራቶችና ስምምነቶችን እንዲያፈላልግና የመንግሥትን ድጋፍ እንዲጠቀም አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG